አስቸኳይ የሕይወት አድን ጥሪ ፡ የልጆች እናት ሕይወት አድን ህክምና ትፈልጋለች
መሰረት ፈንታቢል በባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ እና የሶስት ልጆች እናት ስትሆን፣ በትህትናዋ እና በደግነቷ የምትታወቅ እና ለተቸገሩ ሰዎች የአቅሟን ሁሉ ለማድረግ ግንባር ቀደም የሆነች መልካም ሴት ናት፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ላለፉት ስድስት ዓመታት ለሕይወት አስጊ የሆኑ ከባድ የጤና ችግሮችን ስትታገል ቆይታለች፡፡ ሁለቱም ኩላሊቶቿ ከጥቅም ውጭ በመሆናቸው በ2015 ዓ.ም. የ70 ዓመቱ አባቷ ኩላሊታቸውን ለግሰዋት ንቅለ ተከላ ተደርጎላት ነበር፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ንቅለ ተከላው አልተሳካም። በዚህም ምክንያት ሌላ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ የግድ ያስፈልጋታል፡፡ አሁን በየጊዜው የኩላሊት እጥበት እያደረገች ትገኛለች።
ነገር ግን ከዚህም በላይ የሚያሰጋው ሥር በሰደደ ተጓዳኝ የልብ በሽታ (Chronic rheumatic valvular heart disease) እየተሰቃየች መሆኑ በሃኪሞች መረጋገጡ ነው። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የህክምና ቡድን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ከመደረጉ በፊት የልብ ህመሟ መታከም አለበት ብሏል፡፡ እንደሚታወቀው እንዲህ አይነት የነፍስ አድን የቀዶ ጥገና ህክምና በኢትዮጵያ ውስጥ ሊደረግ ስለማይችል በውጭ ሃገር ማለትም በሕንድ ወይም በታይላንድ መደረግ ይኖርበታል። አጠቃላይ የህክምናው ወጭ ከ50,000 ዶላር በላይ የሚገመት ሲሆን ይህም ለመሰረት እና ቤተሰቧ ከአቅማቸው በላይ ነው።
መሰረት ሕይወቷን ለማዳን የሚያስፈልጋትን ህክምና እንድታገኝ በዓለም ዙሪያ ያሉ ደጋግ ሰዎች እንዲረዷት እና ሕይወቷን እንዲታደጓት በፈጣሪ ስም ትጠይቃለች! እያንዳንዱ መዋጮ ለልጆቿ እና ለቤተሰቧ እንድትኖር እድል በመስጠት ረገድ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።
ስለ ልግስናችሁ፣ ስለ ደግነታችሁ እና ስለ ጸሎታችሁ አስቀድመን በፈጣሪ ስም እናመሰግናለን! ለድጋፋችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
GoFundMe:
https://www.gofundme.com/f/urgent-lifesaving-call-for-meseret-fentabil
የንግድ ባንክ: 1000490056495
አቢሲኒያ ባንክ: 116566141
መሰረት ፈንታቢል
ስ.ቁ. 0924417288

gofundme.com
Urgent Life-Saving Call for Meseret Fentabil, organized by Desalegn Mengistie
አስቸኳይ የሕይወት አድን ጥሪ ለመሰረት ፈንታቢል፡ የልጆች እናት ሕይወት አድን ህክምና ትፈልጋለች
መሰረት… Desalegn Mengistie needs your support for Urgent Life-Saving Call for Meseret Fentabil

#ድምፅ_መስጠት_ተጀመረ!
#አንቴክስ_ፉድ_ኤይድ_ፕላስ ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን የሰላም ዘርፍ እጩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በሰላም ዘርፍ ከአምስት እጩዎች ውስጥ ተክትተዋል የዘርፉ አሸናፊ ከሆኑ #10ሚሊየን ብር ይሸለማሉ!!!
ብፁዕነታቸውን BIWን በማስቀደም ኮድ08 (BIW08) በማስገባት በSMS 9355 ላይ አሁኑኑ ይምረጡ!!!
ድምጽ መስጠቱ እስከ ሐሙስ ታህሳስ 17/2017 ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!
በSMS 9355 ላይ BIW08 በማለት ብፁዕነታቸውን አሁኑኑ ይምረጡ!!!
#10ሚልዮን #አንቴክስ #ፉድኤይድፕላስ #biwsprize #BTM #ብፁዕአቡነኤርምያስ #ይምረጡ
Vote Abune Ermias now for the BIWs prize!
#AbuneErmias
#10million #BIWS2024 #Prize #ANTEXETHIOPIA #ANTEXTEXTILE #FOODAIDPLUS #BESHATUTOLEMARIAMMULTIMEDIA

እንደምን አላችሁ?
የነቢያት ጾም ሰንበታት የራሳቸው ስያሜዎች እንደ ዐቢይ ጾም ያላቸው ሲሆን የነገው ሰንበት ከጌታችን ፱ቱ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው ስያሜውም ስብከት ይባላል!
ለነገው ቅዳሴ እንዲያግዝ የዕለቱ ግጻዌ ከነ ዝማሬው ከelam የቴሌግራም ገጽ በክቡር አባታችን አባ ኃይለ ሚካኤል የተዘጋጀ እናጋራችኋለን፤
መልካም በዓል
መዝሙር ዘስብከት ከታኅሣሥ ፯ - ፲፫
(በ፪/ዩ) ወልዶ መድኅነ ንሰብክ ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ፤ አክሊለ ሰማዕት ሠያሜ ካህናት ወተስፋ መነኮሳት ወልዶ መድኅነ ንሰብክ ወልዶ መድኅነ ንሰብክ
ትርጕም፦
ቅድመ ዓለም የነበረ መድኃኒት ልጁን እንሰብካለን፤ የሰማዕታት አክሊል፣ ካህናትን የሚሾም፣ የመነኮሳት ተስፋ የሆነ መድኃኒት ልጁን እንሰብካለን።
የዕለቱ ምንባባት፦
ዕብ ፩፥፩ - ፍ፤
፪ጴጥ ፫፥፩ - ፲፤
ግብ ፫፥፲፯ - ፍ፤
የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፩፥፵፬ - ፍ፤
ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ
የዕለቱ ምስባክ፦
ፈኑ እዴከ እምአርያም፤
አድኅነኒ ወባልሐኒ እማይ ብዙኅ፤
ወእምእዴሆሙ ለደቂቀ ነኪር። መዝ ፻፵፫፥፯፤
ትርጉም፦
እጅህን ከአርያም ላክ፤
ከብዙ ውኃም አድነኝ፤
ከባዕድ ልጆችም አድነኝ።
ምሥጢር፦
ረድኤትህን ከአርያም ላክ አንድም ልጅህን በሥጋ ላክ፤
ከብዙ ጦር/ሠራዊት አድነኝ አንድም ከፍትወታት እኩያት ከኃጣውእ ርኩሳት ከፍዳ ከመከራ ነፍስ ፈጽመህ አድነኝ።
ከነናምሩድ ከነሳኦል ልጆች እጅ አድነኝ አንድም ከዲያብሎስ ወገኖች ሥልጣን አድነኝ።
ክንድ ከአካል ተገኝቶ ከአካል ሳይለይ ይኖራል፤ እሱም ከአብ ተገኝቶ ከአብ ሳይለይ ይኖራልና። ቦ የሰው ኃይሉ በክንዱ እንዲታወቅ የአብም ኃይሉ በወልድ ታውቋልና። ቦ ክንድ ከአካል ሳይለይ የወደቀ አንሥቶ ይመለሳል፤ እሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አንድነት ሳይለይ የወደቀ አዳምን አንሥቶ ተመልሷልና። ቦ በክንድ የራቀ ያቀርቡበታል የቀረበ ያርቁበታል፤ የራቀ አዳምን አቅርቦበታል የቀረበ ዲያብሎስን አርቆበታልና። ቦ በክንድ አሥረው ያጠብቁበታል ወርውረው ያርቁበታል፤ ዲያብሎስን በእሳት ዛንጅር ይዞ በነፋስ አውታር አሥሮ ከሰው ሕይወት አርቆበታልና። ቦ በክንድ የታሠረ ይፈቱበታል የተፈታ ያሥሩበታል፤ የታሠረ አዳምን ፈትቶበታል የተፈታ ዲያብሎስን አሥሮበታልና። ኋላም ሑሩ እምኔየ ብሎ ያርቅበታል ንዑ ኀቤየ ብሎ ያቀርብበታልና እጅህን ላክ አለ።
መልእክት፦
ዛፍ ከሥሩ ሳይነቀል ጫፉ መሬት ነክቶ ይመለሳል የአምላክ ሰው የመሆን ምሥጢርም እንዲሁ ነው። ምሥጢሩ የዚህን ያህል ጥልቅና ረቂቅ ከሆነ በምሥጢረ ሥጋዌ ዙሪያ አምላክ እንዴት ሰው እንደሆነ ሰውም እንዴት አምላክ እንደሆነ ተመራምሬ እደርሳለሁ ማለት የውቅያኖስን ውኃ በእንቁላል ቅርፊት ቀድቶ ለመጨረስ እንደመሞከር ነው።
©

እንግዲህ እንደነዚህ ያሉትን እወቁአቸው።
1ኛ ቆሮንቶስ 16፥18
His Holiness Karekin II Catholicos of All Armenians, the supreme head of the Armenian Apostolic Church
His Holiness Pope Tawadros II 118th Pope of Alexandria and Patriarch of the See of St. Mark (Coptic)
His Holiness Abune Basilios 6th Eritrean Orthodox Patriarch
His Holiness Abune Mathias Patriarch and Catholicos of Ethiopia, Archbishop of Axum and Echege of the See of Takla Haymanot
His Holiness Mor Ignatius Aphrem II 123rd Patriarch of the Universal Syriac Orthodox Church (Patriarch of Antioch and all of the East)
His Holiness Moran Mar Baselios Marthoma Mathews III Catholicos of the East and Malankara Metropolitan (Indian)

በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም። ኃጢአትን ከፈጸሙና ከሠሩ በኋላ ለኃጢአት ያበቃ ሌላ ምክንያት ማቅረብና በዚያም አንፃር ለመጽናናት መሞከር በራሱ ኃጢአት ነው። በዚህ አይነት ለኃጢአቱ ምክንያት እየደረደረ የሚጽናና ሰው ኃጢአትን እየለመደ ወደ ባሰ አዘቅት ከመውረድ በቀር ንስሐ ለመግባት አይችልም። ምንም ምክንያት ቢደረድር ኃጢአት ምን ጊዜም ኃጢአት ነውና። ለሠራነወ ኃጢአት የተለያዩ ምክንያቶችን በማበጀት ራሳችንን እያጽናናን ነፃ ለመሆን መጣር የለብንም ።
ስለ ሰሩት ኃጢአት ምክንያትን የደረደሩ አዳምና ሔዋንም ባቀረቡት ምክንያት ከመቀጣት አልዳኑም ። እግዚአብሔርም አዳም ስለ አቀረበው ምክንያት "የሚስትህን ቃል ሰምተኻልና ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዘዝኩህ ዛፍም በልተኻልና " በማለት ለኃጢአቱ የሚገባውን ቅጣት ሰጠው እንጂ አልተወውም። [ዘፍ3፥17] ይባስ ብሎ በእነርሱ ምክንያት በመጣው መርገም ቅጣቱ በትውልዳችን ሁሉ ሆነ እንደ እነርሱ ሁሉ እኛም ዘወትር ምክንያት በመደርደር ከኃጢአታችን የተነሣ ከሚመጣው ቅጣት ለማምለጥ የምንሞክር ሆንን ስለዚህ ንስሐ ለመግባት በጣም ስንቸገር እንታያለን ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

ሀለዉ ዝየ ይቀውሙ እለ ኢይጥእምዋ ለሞት
. በዚህ ከቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አሉ
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥
ይኽን ቃል የትህትና አባት ከሆነውና የራሱን ክብር ከመግለጥ ከተቆጠበው ቅዱስ ዮሐንስ በቀር ቀሪዎቹ የከበሩ ወንጌላውያን በክታባቸው አኑረውልናል።
ቅዱስ ማቴዎስ
“እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።” 【ማቴ. ፲፮፥፳፰】
ቅዱስ ማርቆስ
“እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ አላቸው።” 【ማር. ፱፥፩】
ቅዱስ ሉቃስ
“እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከሚቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።” 【ሉቃ. ፱፥፳፯ 】
ቅዱስ ዮሐንስ በምድር ላይ የነበረውን የዘመኑን ፍፃሜ በሚመለከት በሁለት የታሪክ ዘውጎች የሚተርኩ መዛግብትና ሊቃውንት እናገኛለን።
① አንዳንዶች ሞቷል የሚሉ ናቸው፤ ይኸውም በሥጋና ነፍስ መለያየት በሚመጣ ሞት ዐረፍተ ዘመን ገቷቸው ነፍሳቸው በገነት እስከ ትንሳኤ ዘጉባኤ ከምትጠበቅ ጻድቃን ጋር ቅዱስ ዮሐንስም ተደምሯል ይላሉ፤
② ሌሎች ደግሞ ‘የለም’ ቅዱስ ዮሐንስ ልክ እንደ ኤልያስ እንደ ሔኖስ፣ እንደ ዕዝራ … እንደ ሌሎችም ሞት ያላገኛቸው ቅዱሳን ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነቀ በመሆኑ አርጓል ተሠውሯል ይላሉ።
ከዚህ በማስከተል የሁለቱንም ሐሳቦች መነሻ ምክንያቶች እናስቀምጥ
በመጀመሪያ አርፏል የሚሉቱ እንደ ስንክሳር ያሉ መጻሕፍት ድርሳነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና ከውጪ መዛግብት የተገኙ ቀደምት ምስክሮች በአስረጂነት ይቀርባሉ።
✧ «ወበዛቲ ዕለት ዐዕረፈ …» ስንክሳር
✧ «እስመ መብዝኅተ አዕፅምቲሆሙ ለሐዋርያት ኢነአምር አይቴ ውእቱ ወዘያሌቡሰ ላዕለ ዝንቱ ከመ መቃብረ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወዮሐንስ ወቶማስ እሙራን ወክሡታን እሙንቱ» የሚለውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን ፳፮ ንባብ ይዘው ሞቷል ፣ የነፍስ ከሥጋ መለየት አግኝቶት ተቀብሯል ይላሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ አለመሞቱን ለመሞገት «ዐዕረፈ» ፣ «እሙር መቃብሩ» … ያለውን ተቀብለው ግን ይህ መሞቱን እንደማይገልጥ ብዙ አስረጂ እያቀረቡ በመሞገት ዮሐንስ ተሰውሯል ወይም ወደ ገነት አርጓል ይላሉ (ከታች ማስረጃዎቹን እናስቀመምጣለን)
በቅድሚያ ግን ሊቃውንት መምህራኖቻችን በመጻሕፍት እንዲህ ያለ የታሪክ ክፍተት የዘይቤ አለመስማማት ሲገኝ (ለሌሎችም ሐሳቦች ቢሆን) ሁለት መፍትሔ እንዲወሰድ ይመክራሉ።
፩ኛ) ቅድሚያ ለአብያተ ጉባኤ ትርጓሜ የወንበር ትምህርቶች ቦታ መስጠት ብሉያት ሐዲሳት ሊቃውንትና መነኮሳት የምንላቸውን ፬ቱን ትርጓሜ መጻሕፍት ሌሎች የዜማ ቤት የቅዱስ ያሬድ ገጸ በረከቶች እና በቅኔ ቤት የሚነገሩ ታሪኮች ከየቤተ ጉባኤ መምህራን ቀለማት ጋር ማሳተት (ይህ በዘመናችን እንደምናየው አዋልድ መጻሕፍትን እስከማጣጣል የሚደርስ ሳይሆን ቅድሚያ ለማን ቦታ እንሥጥ ሌሎቹን ምን ብለን እናስታርቅ ወደሚለው የሚያሳድግ ነው)
፪ኛ) የዘይቤና የታሪክ ክፍተቶችን በምሥጢር አስታርቆ ማስማማት
ለምሳሌ አንድ ታሪክ ቅድሚያ ቦታ ይሰጣቸው ብለን በጠቀስናቸው መጻሕፍት ላይ ቢገኝና አሁን እንዳነሳነው ዓይነት ከስንክሳሩ ታሪክ ጋር አንድነት ያለው ባይመስል ሊቃውንት እንዲህ የሚል አስተሰናኣዊ (የሚያስማማ) ሐሳብ ያቀርባሉ።
ለምሳሌ በሉቃስ ፪ ላይ የተቀመጠውን የጌታችንን ግዝረት ጉዳይ በማስታረቅ ሊቃውንት እንዴት ሐተታውን እንዳስቀመጡልን እንመልከት
« ዮሐንስን የሊቀ ካህናት ልጅ ነው ብለው አክብረው ሊገዝሩት መጡ አለ፤ ጌታ ግን መምጣቱ ለትሕትና ነው እንጂ ለልዕልና አይደለምና ወሰዱት አለ፣ ሃይማኖተ አበው “ዝንቱ ዘተገዝረ አመ ሳምን ዕለት ዝንቱ ዘገዘርዎ በሥርዓተ ሕፃናት” ይላል። ስንክሣር “አልተገዘረም” አለ። እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም! ። ስንክሣር ምን ቁም ነገር ነው ፣ ነገር እንደ ሃይማኖተ አበው ነው፤ ይህስ ስንክሣርን መንቀፍ ሃይማኖተ አበውንም መንቀፍ ነው መላሻቸው አንድ ነው ብሎ። ገዛሪው ምላጭ ይዞ ቀርቧል ወዳጄ ልትገዝረኝ መጣህ ቢለው ምላጩ እንደ ሰም ቀልጦበታል ከዕለተ ዓርብ አስቀድሞ ደሙ አይፈስምና እሱ በተአምራት ተገዝሯል። ሃይማኖተ አበው መገዘሩን ሲያይ ተገዘረ አለ። ስንክሣር በገዛሪ እጅ አለመገዘሩን ሲያይ አልተገዘረም አለ።"
በዚህ አገላለጽ ውሥጥ ስንክሳር ምን ቁም ነገር ነው? ነገር እንደ ጉባኤ ቤቱ መጻሕፍት (ሃይማኖተ አበውን የመሰሉ) ነው እንጂ! ይልና የለም ይህስ ስንክሳርን መንቀፍ እንደ ሃይማኖተ አበው ያሉ ደገኛ መጻሕፍትን አብሮ መንቀፍ ነው ምክንያቱም መላሻቸው ፣ መነሻቸውም ፣ ምንጫቸው አንድ ነው ሁሉም አምላካውያት መጻሕፍት ናቸውና ብሎ ማስታረቅ ይገባል እንጂ! ይላል። ስለዚህ ያ በዚህ ምክንያት ይህ ደግሞ በዚህ ምክንያት ትክክል ነው ብሎ መጽሐፍ በመጽሐፍና በተጠያቂ ሊቅ ይዳኛል ማለት ነው።
የዛሬውን መነሻ ርእሰ ጉዳይ በዚህ መንገድ አስቀምጠን ሁለቱንም አክብሮ በማስታረቅ ወደ አንድ የጋራ ሐሳብ መምጣት ተገቢ መንገድ ይሆናል።
✧ በቅድሚያ ሐሳቦቻችንን አስረጂ በመጥቀስ እናጠናክራቸው
ሀ】ከወንጌል የተገኘ ምስክርነት ፩
ተከታዩን የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል ልብ ብለን እናንብብ
【የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩ ከቁጥር ፳ እስከ ፳፫ 】
"ጴጥሮስም ዘወር ብሎ ኢየሱስ ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ እርሱም ደግሞ በእራት ጊዜ በደረቱ ተጠግቶ፦ ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው? ያለው ነበረ። ጴጥሮስም ይህን አይቶ ኢየሱስን፦ ጌታ ሆይ፥ ይህስ እንዴት ይሆናል? አለው። ኢየሱስም፦ እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ፥ ምን አግዶህ? አንተ ተከተለኝ አለው። ስለዚህ፦ ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም የሚለው ይህ ነገር ወደ ወንድሞች ወጣ፤ ነገር ግን ኢየሱስ፦ እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ? አለው እንጂ አይሞትም አላለውም"
ከዚህ ክፍል "እመኬ ፈቀድኩ የሀሉ እስከ ሶበ እመጽእ ሚ ላዕሌከ⇨ እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ" የሚለውን መተርጉማን ያስቀመጡት አልሞተም አንድም ሞቷል ሸሚል መንገድ ነው፤
«እኔ ከወደድኩ እስክመጣ ቢኖር ምን አግዶህ አለው እንጂ አትሞትም አላለም። ዮሐንስ ሞቷልን አልሞተም ቢሉ አልሞተም። ይህ እንዳይሆን ሊቁ «መቃብረ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወዮሐንስ እሙራን ወክሡታን እሙንቱ» ይላል ብሎ ሞቷል። ይህም ሊታወቅ መላእክት መቃብሩን ቆፍረዋል ከመቃብሩ ገብቶ ሲጸልይ ደቀ መዝሙሩን ፋጊርን (አብሮኮሮስን?) የኤፌሶንን ሰዎች በተማራችሁት ትምህርት ጸንታችሁ ኑሩ ብለህ ንገራቸው ብሎ ላከው ነግሮ ቢመለስ መቃብሩ የለፋ መስክ ሁኖ አጽፉን መቋሚያውን መነሣንሡን ከዳሩ አግኝቶታል።»
ስለዚህ መደረቢያው በትሩና ጭራው መገኘቱ መቃብር ሳትይዘው ለመውጣቱ በአስረጂነት ይቀርባል። በንባቡም ጌታው እስኪመጣ ድረስ እንዲኖር ወዷል ለሞቷል ባይ "ቢኖር ምን አግዶህ?» የሚል መልስ በባለቤቱ መሠጠቱን ማስተዋል ይገባል። ተሰውሯል የሚሉቱም ቢሆኑ አይሞትም (ወደፊት) ሳይሆን አልሞተም ባዮች መሆናቸውን ልንረዳ ይገባል።

St. John the Evangelist Orthodox Church
Our Patron Saint - St. John the Evangelist Orthodox Church
The Holy, Glorious All-laudable Apostle and Evangelist, Virgin, and Beloved Friend of Christ, John the Theologian was the son of Zebedee and Salome, a daughter of St Joseph the Betrothed. He was called by our Lord Jesus Christ to be one of His Apostles at…
ለ) ሁለተኛው ከላይ በመነሻነት የተቀመጡ የሦስቱን ወንጌላውያን መልእክት ስናነብ በመጽሐፍ ቤት የሐዲሳቱ ሊቃውንት ደብረ ታቦር አልፎ በተናገረበት አውድ ሲፈቱ ትርጓሜውን ለዮሐንስ ሰጥተው «የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች» የተባለው እርሱን የሚወክል እንደሆነ ነግረዋል
አንዳንዶች ብሎ ማብዛቱ መጽሐፍ ስም ካልጠራ ማብዛት ልማዱ ነውና
ለምሳሌ ፦ በተአምኖ አመ ነገርዎ ለኖኅ (የነገረው አንድ መልአክ ሆኖ ሳለ) ፣ ብፅዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ዘነገሩኪ (ያበሠረው አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ሆኖ ሳለ)
በሌላ መልኩ ደግሞ በተቀሩት ሦስቱ ወንጌላውያን ተጠቅሶ በእርሱ አለመጻፉ ራሱን የሚመለከት ቢሆን ነው። ክብሬ ይገለጥልኝ መወደዴ ይነገርልኝ ብሎ ጉዳዩ እርሱው ራሱ ባለበት ተነግሮ ግን በወንጌሉ ሳያኖርልን የቀረው ስለትህትና እንደሚሆን ይታመናል።
ሐ) ደብረታቦርን ካነሳን እግረ መንገድ ቅዱሱ አባታችን ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ምሥጢረ ታቦርን ደጋግሞ ከአማናዊት የሐዲስ ኪዳን መርጡል ጋር እያዛመደ አስተምሮበታል። በሥፍራው የተገኘውን አልያስን አንስቶ ወደብሔረ ሕያዋን እንዴት እንደተነጠቀ ሲነግረን «ወከበቶሙ እግዚአብሔር ውስተ ምድር ኅብእት እንተ ተሠወረት በጥበበ ዚኣሁ ወአልቦ ሥልጣነ ሞት» ይላል።
ታዲያ መሰሉን አብነት ይዘው መምህራን በቦታው የተገኘውን ኤልያስ ከዮሐንስ እንድናነጻጽር በማመላከት፤ አምላካችን ክርስቶስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ በመስቀል ተሰቅለው ቢያልፉ ፣ ሊቀ ነቢያት ሙሴና የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብ በዕረፍተ ሰላም ይኽን ዓለም ቢሰናበቱ፤ ታላቁ ነቢይ ኤልያስና ተወዳጁ ደቀ መዝሙር ዮሐንስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተጠርተዋልና… በኋላው መንገዳቸው ያላቸውን ተዛምዶ ሊያሳይ አወዳጅቶ አገናኛቸው ተገናኛቸውም ይላሉ።
መ) ከዜማ ቤቱ ደግሞ ዮሐንስን በብሔረ ሕያዋን አየሁት የሚለን ቅዱስ ያሬድ ነው። በድጓው ደጋግሞ ምስክርነቱን ሠጥቶናል
«ይኔጽር ዓየራተ
ይነግር ኅቡዓተ
እንዘ ይጽሐፍ በእደዊሑ ዘወንጌል ቃላተ
በቅናተ እግዚኡ ሐቌሁ ቀነተ
ዮሐንስ ድንግል ዘኢጥዕመ ሞተ »
【ከምድር በላይ ጠፈሩን ይመለከታል ፣ የተሰወረውን ይናገራል በእጆቹ የወንጌልን ቃል እየጻፈ በጌታው መታጠቂያ ወገቡን ታጠቀ ፤ በንጽሕና የኖረው ድንግል ዮሐንስ ሞትን ያልቀመሰ ነው! 】
【በድጓ በግእዝ አርያሙ ክፍል ለጥር ፬ቱ ቁመት መነሻ እንዲሆን የጻፈልን ነው። ብራና ገጽ ፻፺፩】
ቅዱስ ያሬድ በሌላም ሥፍራ ከሞት ተለይቶ እንደመላእክቱ በሕይወት አለ ሲል ዳግመኛ ምስክርነቱን እንዲህ እያለ ያጸናዋል «በንጽሕ ከመ መላእክት ተሠርገወ ወእመዊት ከማሆሙ ሐይወ » 【እንደ መላእክቱ ንጽሕናን የተሸለመ ነው ከሞቶም ተለይቶ እንደነሱ በሕይወት አለ】
ሠ) በመልኩ ክፍልና በገድለ ሐዋርያት ማጠቃለያ እንዲሁም በስንክሳራችን የመሰወሩ ምስክርነት ተቀምጦ እናገኛለን
መልክአ ፍቁረ እግዚእ በመጨረሻዎቹ ሁለት ክፍሎች እንዲህ የሚል ድርሰት እናገኛለን ፦
« ሰላም ለፍልሰትከ ዮሐንስ ሕያው፤
በከመ ወፅአ ነገር እምኀበ አኃው፤
በቅድስና ወበንጽሕ አባላቲከ ሥርግው፤
አብሀኒ ለነሶሳው በውሳጤ ገነት ፍትው፤
ኀበ ይነብሩ ስንዓ ኅሩያን ዕደው።»
【 በወንድሞች ዘንድ አይሞትም የሚለው ይህ ነገር ወጣ እንደተባለ ያልሞትህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! ለፍልሰትህ ሰላምታ ይገባል፤ በቅድስና እና በንጽሕና ሰውነቶችህ የተጌጡ ናቸው፤ በሚወደድ በገነት ውስጥ ለመመላለስ አሰልጥነኝ/አብቃኝ፤ በዚያ የሚኖሩ የተመረጡ ወገኖች ናቸውና።】
«ሰላም ለልብስከ ወለአሣእኒከ ደርገ፤
ተዝካረ ሕይወትከ ያዑቅ ለአብሮኮሮስ ዘተኃድገ፤
ዮሐንስ ዘኮንከ ምስለ መላእክት ዘውገ፤
ምሉዓ ወድግዱገ ዘሰላምከ ፈለገ፤
በውሣጤ ከርሥየ ኢይኩን ንቱገ፡፡ »
【የመኖርህን ነገር ያስረዳ ዘንድ ለተተወ ፤ ለልብስህ ከጫማህ ጋር ክብር ይገባል፤ ከመላእክት ጋር ወዳጅ የሆንክ ዮሐንስ ሆይ! ሞልቶ የተትረፈረፈ የፍቅር አንድነትህ ወንዝ በሆዴ ውስጥ የጎደለ አይሁን /ይሙላ/።】
ከላይ በተመለከትናቸው የመልክእ ምስጋና ክፍሎች ውሥጥ ቀደምት አበው ሞትን ሳይቀምስ መፍለሱን ወደብሔረ ህያዋን መድረሱን አስረግጠው አኑረዋል፤ በገድሉም በስንክሳሩም የተነገረው ከዚሁ ጋር አንድ ነው
«ወሶበ አእመረ ብፁዕ ዮሐንስ ከመ ቀርበ ፍልሰቱ እምዝንቱ ዓለም ፀውዖሙ ለሕዝብ ወሠርዐ ቍርባነ ወመጠዎሙ ምሥጢራተ ቅድሳት ወአዘዞሙ ከመ ይፅንዑ ውስተ ሃይማኖት ርትዕት ወናዘዞሙ ወባረኮሙ። ወእምዝ አዘዞ ለረድኡ አብሮኮሮስ ወለ፪ቱ ላእካን እምአኀው ከመ ይንሥኡ መካርየ ምስሌሆሙ ወይትል ውዎ ወወፅአ ኀበ አፍአ ሀገረ ኤፌሶን ንስቲተ ወአዘዞሙ ከመ ይክርዩ ግበ ወወረደ ውስተ ግብ ወአውፅአ አልባሲሁ እምላዕሌሁ ወኢተርፈ ላዕሌሁ ዘእንበለ ፩ ቀሚስ ዘሰንዱን። ወአንሥአ እደዊሁ ውስተ ሰማይ ወጸለየ ወአስተፋነዎሙ ከመ ይትመየጡ ውስተ ሀገር ወይንግርዎሙ ለአኀው ከመ ይፅንዑ ውስተ ሃይማኖት ዘክርስቶስ። ወይግበሩ ምግባራተ ሠናያተ እስመ ሀለዎ እግዚአብሔር ይፈድዮሙ ለኵሎሙ ለለ፩ በከመ ምግባሮሙ። ወይቤሎሙ ካዕበ ንጹሕ አነ እምደምክሙ እስመ ኢያንተጉ ምንተኒ እምት እዛዛቲሁ ለእግዚአብሔር ልዑል ወእም ኵሉ ሥርዓቱ ዘይደልወክሙ ወአንትሙ እምይእዜ ኢትሬእዩኒ ገጽየ ግሙራ። ወሶበ ይቤ ዘንተ በከዩ ወተአምኁ እደዊሁ ወእገሪሁ ወኀደግዎ ውስተ ግብ ወሖሩ ውስተ ሀገር ወነገርዎሙ ለኵሎሙ አኀው። ወሶበ ሰምዑ ነደ ልቦሙ በኀዘን ወሮፁ ወኀሠሥዎ ወኢረከቡ መቃብረ አላ ረከቡ አሣእኖ ወ፩ ልብሶ። ወሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ወአንከሩ ምግባራቲሁ ዘአ ዕረፎ ለረድኡ ዮሐንስ በዝንቱ ዕረፍት ሠናይ።»
【የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም ። ከዚህም በኋላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ። ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጕድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም ። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና ። ሁለተኛም እንዲህ አላቸው እኔ ከሁላችሁም ደም ንጹሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩኝም ። ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ። 】
ረ) የሊቃውንት ቅኔ ለጊዜው በዝክረ ሊቃውንት ከተዘገቡት ሁለቱን ልጠቁም (ጉባኤ ቃናና ዘአምላኪየ)
«ዘማ መቅበርት ለወልደ ነጎድጓድ ትቤሎ፤
እመ ትጸልአኒ አንተ ዘያፈቅረኒ ሀሎ»
(ዘማ የሆነች መቃብር ዮሐንስን እንዲህ አለችው አንተ ብትጠላኝም የሚያፈቅረኝ አለኮ)

« ወልደ ነጐድጓድ ተሰደ እንዘ የኀድግ ሀገረ፤
እምኅበ አጥፍአ ሞተ ሰብእ ሦረ፤
ገራህቱ መቅበርት አምጣነ አብቈለት ሣዕረ»
ሰ) ከውጭ የተገኙ ቀደምት ምንጮች
በውጭ ሀገራት ቀደምት ድርሳናትና ሊቃውንትም ዘንድ ቢሆን ከላይ ያነሳነውን ጭብጥ የሚደግፍ ታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።
https://www.stjohnaz.org/about-us/our-patron-saint/#:~:text=He%20bade%20them%20prepare%20for,disobedient%2C%20they%20fulfilled%20his%20bidding.
በሌላ ሥፍራ የተገኘው ደግሞ ይህን ይላል ቅዱስ ዮሐንስ የሚነጠቅበት ሠዓት እንደደረሰ ሲያውቅ በመስቀል ቅርጽ የተሰናዳ መቃብር እንዲያዘጋጁለት አርድእቱን አዟል እነርሱም በበዛ እንባ መምህራቸውን እየሳሙ ካለመታዘዝ እንዳይቆጠርባቸው ፊቱን በጨርቅ ሸፍነው ወደ መቃብሩ ሥፍራ አኑረውት ሄደዋል። ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ( ቅዱስ አብሮኮሮስ) ወደቦታው ተመልሶ ቢመጣ መቃብሩን ቢከፍተው ባዶ ሆኖ አግኝቶታል።
«He bade them prepare for him a cross-shaped grave, in which he lay, telling his disciples that they should cover him over with the soil. The disciples tearfully kissed their beloved teacher, but not wanting to be disobedient, they fulfilled his bidding. They covered the face of the saint with a cloth and filled in the grave. Learning of this, other disciples of Saint John came to the place of his burial. #When_they_opened_the_grave, they found it empty.»
በአብሮኮሮስ ስለተሠጠው ምስክርነት (testimony of St. Prochorus) ደግሞ ተከታዩት አስረጂ በሊንኩ ታግዘው ቢያዩ የበከጠ ሐሳባችንን ያግዛል።
https://www.johnsanidopoulos.com/2009/09/repose-of-st-john-theologian-according.html?m=1
ከዚህ በዘለለ ጽንፍ አንዳንዶች ደግሞ ዛሬ መቃብሩ ባለበት አጽሙ የማይገኘው ከጌታችንና ከእመቤታችን ቀጥሎ የትንሳኤ ዘለክብር ባለቤት ሆኖ ዕለተ ምጽኣትን ሳይጠብቅ እሱም ከሙታኑ ተለይቶ የተነሳ ስለሆነ ነው የሚል ትውፊት አላቸው፤ ይህንንም ትንሳኤ Metastasis እያሉ በመግለጥ ዐመታዊ ዕለተ ትንሳኤውን በወርኃ መስከረም ያከብራሉ!
According to Holy Tradition, the reason we have no physical remains but rather an empty tomb of the Apostle John is because when the disciples returned to his tomb, it was found empty. It is assumed that he was raised, just like the Lord and the Theotokos. This is what we call "Metastasis" (Translocation or Transposition), and it is what we celebrate on September 26th.
✧ ሞቷል ለሚለውስ በማስታረቂያነት ምን ሐሳብ ማቅረብ ይቻላል?
በኤፌሶን/ ቱርክ የመቃብሩ ሥፍራ ይህ ነው እየተባለ ዛሬም ለጎብኚዎች ይታያል።
ይሁንና ግን ከላይ እንዳየነው
☞ ገራህቱ መቅበርት አምጣነ አብቈለት ሣዕረ ፣
☞ልብሱ ለዮሐንስ ወአሣእኑ ዘተኃድገ ለአብሮኮሮስ ከመ ያዑቅ ሕይወቱ ፣
☞ When they opened the grave, they found it empty… በማለት መቃብሩ እንጂ የተቀባሪው የከበረ ሥጋ በቦታው አለመገኘቱ ተነግሯል፤
አስቀድሞ በመላእክት ቢሉ በደቀመዛሙርቱ መቃብሩ መዘጋጀቱ እውነት ቢሆንም ሥጋው ከዚያ መታጣቱና የአብሮኮሮስ ምስክርነት ተሰውሯል ወደሚለው ያደርሰናል።
በአንዳንድ የስንክሳር ቅጂዎችና ድርሳናት አዕረፈ ☞ ሞተ የሚል አገላለጥ እናገኛለን ፤ ይህን በሚመለከት ወደ ብሔረ ሕያዋን ተነጥቀዋል ብላ ቤ/ክርስቲያን የምትናገርላቸውን ቅዱሳንን አዕረፈ ብሎ ማስቀመጥ በአያሌው የተለመደ ሆኖ ይታያል። ዐረፈ የሚለው በአገባቡ ሞትን ብቻ አይገልጥም ከዚህ ዐለም ድካም መለየትን ካለንበት ዓለመ መሬት (ምድር) በሕይወት ወደ ብሔረ ብፁዓን አልያም ብሔረ ሕያዋን መሻገር ዕረፍት፣ ከጣር ከገኣር መለየት ተብሎ ሊነገር እንደሚችል ማጤን ይገባል።
የሌሎቹን አበው ወደብሔረ ሕያዋን መሔድ ዕረፍት ይለዋል
ለአብነት ግንቦት ፲፩ ስለ ቅዱስ ያሬድ ሲናገር «በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳያቸው ኢትዮጵያዊው ማሕሌታይ ያሬድ ዐረፈ» ይላልና።
ሌላው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያው ግዛቱና ሀገረ ስብከቱ ቁስጠንጥንያ ለኤፌሶን አጎራባች (ዛሬ ሁለቱም በቱርክ ያሉ አውራጃዎች ናቸው) በመሆኑ የበዛውን የቅዱሳን አጽማቸው የት እንዳለ አናውቅም ነገር ግን የታወቁ የቅዱስ ጴጥሮስ የቅዱስ ጳውሎስ የቅዱስ ቶማስና የቅዱስ ዮሐንስ መቃብራቸው በእኛ ዘንድ አለ ሲል በ፳፮ኛው ድርሳኑ ላይ አስፍሯል «እስመ መብዝኅተ አዕፅምቲሆሙ ለሐዋርያት ኢነአምር አይቴ ውእቱ ወዘያሌቡሰ ላዕለ ዝንቱ ከመ መቃብረ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወዮሐንስ ወቶማስ እሙራን ወክሡታን እሙንቱ»
ታላቁ ቆስጠንጢኖስ በዘመኑ ከፈጸማቸው ደገኛ ተግባራት አንዱ አጊዮ አፖስቶሊ (Ἅγιοι Ἀπόστολοι) የሚባለውን
የቅዱሳን ሐዋርያት መካነ መቃብር ያለበት ቤተመቅደስ ገንብቶ የሁሉንም ሐዋርያት አጽማቸውን በአንድ ቦታ ለመሰብሰብ ጥረት አድርጎ ነበር፤ ይሁንና ግን የቅዱስ እንድርያስና የቅዱስ ሉቃስ እንዲሁም የቅዱስ ጢሞቴዎስ ብቻ ሥጋ በቦታው ለማኖር ችሏል። መቃብራቸው ቢገኝም ተቀባሪዎቹ አለመገኘታቸውን ማወቅ ይገባል።
እንደመውጫ ቅዱስ ዳዊት “ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ ሞትንስ የማያይ ማን ነው? ነፍሱንስ ከሲኦል እጅ የሚያድን ማን ነው?” ይላል【መዝ ፹፱ ፥፵፰ 】ከሰው ወገን ሕያው ሆኖ ለዘለዓለም ነዋሪ ሞትንም ሳያይ በምድር ላይ ቀሪ የሆነ ማንም የለም። የሐዋርያው ክብርና ቅድስናም ከመሞቱ አልያም ወደ ብሔረ ሕያዋን ከመነጠቁ ጋር በቀጥታ የሚያያዝበት ልኬት የለውም። ባለመሞቱ የሚከብርበት በመሞቱ የሚቀርበት መንገድ ስለሌለ ክርስቶስ አይሞትም አላለም እስክመጣ ቢኖር… አለ እንጂ።
ሰው ሕያዊት ነፍሱበ በሞት ከተለየችው እንደፈሰሰ ውኃ ነው
ፈሶ የታፈሰ ውኃ 【ማይ ዘገብኣ እምድኅረ ተክዕወ】
የቅዱሱ መጽሐፍ ብሂል እንዲህ ይላል "ዘእምከመ ተክዕወ ማይ ውስተ ምድር ኢይትገባእ" እኛም እንጂ ይህን ይዘን «የፈሰሰ ውኃ አይታፈስም» እንል የለ!?
【፪ኛ ሳሙ፲፬፥፲፬ 】
ዮሐንስ ግን ሞቶ ተቀበረ ሲሉት ተነስቶ የተነጠቀ ነውና የታፈሰ ውኃ ነውና "ማይ ዘገብኣ እምድኅረ ተክዕወ" አልነው።
ሞተ የተባለ በሰዎች ኅሊና የተቀበረውን ማንነታችን ወደልዕልናው በቸርነቱ ይንጠቅልን
ሎቱ ስብሐት ለዘበስብሐተ አቡሁ ይሴባሕ፤ ወሎቱ ቅድሳት
ለዘበቅድሳተ መንፈሱ ይትቄደስ 🙏
☞ Edited & Яερõšтεδ ƒrõ๓ ጥር ፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.

#በይረሙን (የዛሬው የዕለተ ዓርብ የተለየ ጾም ጉዳይ)
᯼͞᳀͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͞ ͟͞ ̸ ͟͞ ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᳀᯼
✧ "በይረሙን" ምንድር ነው?
መጽሐፈ ስንክሳራችን የጥር ፲ ተዝካር የጥምቀቱን ዋዜማ መታሰቢያ ስለ «ጾመ ዕለት ዋሕድ ⇨ ዘስሙ ገሀድ» በቁጥር ፬ ሲገልጥ እንዲህ ብሏል ፦
☞ ወለእመ ኮነ በዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሑድ ይጹሙ በዕለተ አርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት!
☞ በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን [በይረሙን ያለውን አማርኛው «ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው» ብሎ ይፈታውና] በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ!
☞ And if the day of Bayramum fall on the First Day of the week, or on the Sabbath of the Jews, one shall fast on the Fourth Day of the week [friday] preceding it until the evening!
ታዲያ በዘንድሮው ልክ ስንክሳሩ እንዳስቀመጠው በይረሙኑ ቅዳሜ ስለዋለ ዓርብን ሠዓት ጨምረን መጾም እንዳለብን ልንረዳ ይገባል።
#በ_ይ_ረ_ሙ_ን
በሰዋስው ሊቅነት በሀገራችን ቀድመው የሚወሱት ኪዳነ ወልድ (በመጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ) እንዲኽ የሚል ፍንጭ ያስቀምጣሉ ለበይረሙን መነሻው አረቢኛው በራይም ሲሆን ትርጉሙ ቅድሳት፣ ዕለተ ቅድሳት፣ አስተርእዮ ጥምቀት ማለት ነው ብለው እንደ ምንጭ ስንክ ጥር ፲ን ተመልከት ይላሉ!
ይኽን ይዞ የውጪውን መዛግብተ ቃላት የሚያካልል ቢኖር ከዚህ መድረስ ይችላል በትርጉም በይረሙን ያለው በረይሙን [Baraymun] የሚለውን ሲሆን የአረቡ ባራሙን baramun በግሪኩም παραμόνη ፓራሞን (ፓራሞኔ) በሚል አቻ ትርጉም ቃሉ መታወቁ ተገልጧል!
☞ Comparative dictionary of Geʻez (classical Ethiopic) : Geʻez-English / English-Geʻez, with an index of the Semitic roots /. by Wolf Leslau. Page 109
የአፍሪቃ ድንበር፣ መካነ ጻዕር፣ ልሳነ ባህር… የሚሰኙት ግብጣውያኑ የቅብጥ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቃላትን ምንነት [Dictionary of Church Terms] በዘገቡበት ድረ መካን ላይ ፓራሞን (Paramone)
የሚለውን ቃል ከነ ሥርዓተ በዓሉ በተከታዩ መንገድ አብራርተውልናል!
↳ A Greek term meaning watch, vigil, especially on the eve of a festival. Its Arabic equivalent, Paramun, is a term generally used for the vigils of the Nativity of Our Lord Jesus Christ and of the Epiphany. It is a fast requiring abstention from eating fish, meat, eggs, milk, butter, and cheese. If the day before the feast happens to be Saturday or Sunday, then the paramone begins on Friday because it is not permitted to fast on Saturday or Sunday.
↷ ፓራሞን የግሪክ ቃል ሲሆን መጋድ (ገሃድ መሆን መታየት መገለጥ) ፣ ዋዜማ ይልቁንም ደግሞ የክብረ በዓሉ ፊተኛው ቀን የሚውል ዕለት ተብሎ ይገለጣል። የአረቢኛው አቻ ቃል ፓራሙንም በአጠቃላይ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደትና በዓለ ጥምቀት ዋዜማ የሚነገር ከዓሣ ከሥጋ ከእንቁላል ከወተት ከቅቤና ከአይብ መከልከልን የሚጠይቅ የጾም ቀን ነው! ታዲያ ክብረ በዓሉ አስቀድሞ የሚውለው ይኽ ዕለት በቀዳሚትና በእሑድ ሰንበታት ላይ ያረፈ እንደሆን ፓራሞኑ የሚጀምረው ዕለተ ዓርብ ይሆናል ምክንያቱም በሰንበታቱ ከጥሉላቱ እንጂ ጨርሶ ከመባልዕት መከልከል አይፈቀድምና!
#የበይረሙን_ጦም?
ስንክሳራችን “ይጹሙ በዕለተ ዓርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት! … በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ" ይላል! ተጨማሪ ሰንበታቱን በሚመለከት ዓርብን ጦመናል ብለን ጥምቀቱ (ጥር ፲፩) እሑድ ሲውል ቅዳሜ እንዳንበላ ሰኞ ሲውል ደግሞ እሑድ እንዳንበላ «ይትዓቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ… ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ» ይላል! (ጥሉላት ማለት ቅባታማ ሥጋ ቅቤ ዕንቍላል ወተት የሰባ የድሎት ምግብ…የእንሰሳት ተዋፅኦ የሚለውን ይገልጣል)
በአጭሩ ዘንድሮ በዓሉ የዋለው እሑድ ነው! ስለዚኽ ጦመ «በይረሙን» የሚባለው ቅዳሜን ከጥሉላት መከልከልና ዓርብን ግን እስከ ምሽት ከምግብ መከልከል! (ይኽ ግን በሌላ ዓመት ደግሞ እንዲኹ በዓሉ ሰኞ ቢውል ቅዳሜን ከምግብ ተከልክሎ መዋል ስለማይገባ በተመሳሳይ ዓርብን እነደዚሁ እስከ ምሽት ሳይበሉ መቆየት የሚለውን ይገልጣል!

"ወቀዊሞ ማዕከለ ሕያዋን ወሙታን ከተረ መዓተ"
【መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፲፰ ቁጥር ፳፫】
°✞°°°°°°°°°°°°°°°✥°°°°°°°°°°°°°°°°†°(#ነገረ_ከተራ)
«አሁንስ አበዛችሁት!» ይላሉ ዳታንና አቤሮን እንዲሁም ሐሳባቸውን የገዙ ቆሬና ልጆቹ【ዘኁ. ፲፮፥፫】 የዛሬዎቹን ‘ሁላችን የሀዲስ ኪዳን ካህናት ነን’ ባዮቹን መስለውና በሙሴ ፊት በመቆም
‘አሮንን ብቻ ማን ካህን አደረገው እኛስ ካህን ለመሆን ምን ያንሰናል?’ እያሉ
ጨምረው እንዲህ ይላሉ «ማኅበሩ ሁላቸውም እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸው» ወይ መመሳሰል እንዴት ይደንቃል! ራሳችሁን ቅዱሳን ቅዱሳን እያላችሁ የምትጠራሩና የምትንጠራሩ ደቂቀ ዳታን ውሉደ አቤሮን ኧረ አድቡ። በእግዚአብሔር ምርጫ ላይ አፍ የሚከፍቱትን መሬት ተከፍታ ውጣቸዋለች እኮ!
ዛሬ በውሥጥ በውጪ የቸገረ ነገር የሆነው እንዲህ ዐይነቱ ግብረ ዕቡያን ነው።
⇄ በውሥጥ «አሁንስ እጅግ አበዛችሁት!» እያሉ ከመንበረ ፓትርያርክ ውጪ <መንበረ ሃሮ ዘኦሮሚያ> እና <መንበረ አክሱም ዘትግራይ> እያሉ ራሳቸውን በየሰፈራቸው የቀባቡና የተቀባቡ በሥልጣነ መለኮት ላይ የተሳለቁ የጥምቀት ማግሥት ጉዶች አየን።
⇆ በውጭ ክርስቲያን ነን የሚሉ ደፍረው ራሳቸውን ቅዱስ እያሉ የጠሩ ባለክህነት ለመሆንስ ማን ከልክሎን ብለው በዘፈቀደ የሚሿሿሙ!
ውጤቱ ምን ነበር?
ሙሴ ለቆሬ ልጆች «እጅግ ያበዛችሁትስ እናንተ ናችሁ» 【ዘኁ ፲፮፥፯】እኛ አልከለከልናችሁ ተፈቀደልን ካላችሁ በሉ ከእግዚአብሔር ጠይቃችሁ አግኙት አላቸው ፤ እነ ሙሴ እነ አሮነን ተሰበሰቡ በጉዳዩ ወደ እግዚአብሔር አመለከቱ ከዚያ ጠሯቸው « አንመጣም! በእኛ ላይ ራስህን አለቃ ታደርጋለህ?" አሉ 【ዘኁ ፲፮፥፲፪/፲፫】
አወይ መመሳሰላችን እናንተዬ። ዛሬም አስኬማውን ከማጀት እንደተገኘ የቤታቸው ድስት አጥልቀው በየጎሳቸው የሚሮጡ ሲጠሩ እምቢኝ ብለው በየጓዳው የሚቀላውጡ አቤሮናውያን አየን።
ብቻ ተክህነናል ያሉቱ መሬት ተከፍታ ዋጠቻቸው 250ዎቹን አጣኝ ነን ባዮች ደቂቀ ቆሬና 14,700 ተከታዮቻቸውን መቅሰፍት እሳት ከሰማይ ወርዳ በልታቸዋለች።
ያን ጊዜ ካህኑ አሮን ወደቀሩት ሕያዋን መቅሰፍት እሳቱ እዳይሻገር ከሙታኑ መንደር እንዲቀር በመካከል ቆሞ ያጥን ጀመር ያን ጊዜ #ከተራ_ሆነ። ‘ወበማዕከሎሙ ቀዊሞ ከተረ መዓተ’ ይለዋል።
“በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተከለከለ።” 【ዘኁ ፲፮፥፵፰】
ጠቢቡ ሰሎሞን ላለፈው የካህኑ አሮንን ለሚመጣው የሊቀ ካህናቱ የክርሰቶስን አይቶ ነገሩን እንዲህ እያለ በጥበብ መጽሐፍ ያስተምርበታል።
"ወቀዊሞ ማዕከለ ሕያዋን ወሙታን ከተረ መዓተ
አኮ በኃይለ ሥጋ ወኢበግብረ ንዋየ ሐቅል አላ በቃለ ዚአከ በዘአዘከረ ሎቱ መሐላ አበው ወኪዳኖሙ ☞ በሥጋዊ ኃይልና ለጦርነት በሚሆን መሣርያ አይደለም በራስህ ቃል ለቅዱሳን አበው የማለውን መሐላ የገባላቸውን ቃልኪዳን አስቦ በሞታንና በሕያዋን መካከል ቆሞ መዓቱን ከተረ/አቆመ " 【ጥበ. ፲፰፥፳፫】
የቀደመው አሮን በሙታኑና በሕያዋኑ መካከል ቆሞ "ተዘከር አብርሃምሃ ወይስሐቅሃ ወያዕቆብሃ ዘመሐልከ በርእስከ ☞ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ በራስህ የማልከውን መሐላ አስብ" እያለ መዓቱን ከለከለ መቅሰፍቱን አቆመ። ከተራ ይለዋል እንዲህ ያለውን የመዓቱን መቆም የምሕረቱን መምጣት!
ቀዳማዊና ደኃራዊ ፊተኛውና ኋላኛው ዘልዓለማዊው የሐዲሱ ኪዳን ሊቀ ካህናት ክርስቶስ "የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሟል" ተብሎ በበረኛው በዮሐንስ መጥምቅ የተመሰከረለት የነፍሳችን እረኛ በጥምቀቱ በኦሪታውያኑ ምውታንና በሀዲስ ኪዳኑ ሕያዋን መካከል ቆሞ በቁጣው እሳት በአዳም ዘር ላይ የነደደውን መርገማችንን ደምስሶ መዓቱን በምሕረት መልሶ ባርነቱን አቆመልን። ይህ #በጥምቀቱ_የተገኘ_ከተራ ነው።
① የበጉ እናት የሊቀ ካህናቱ ወላዲት እመቤታችን ድንግል ማርያም ስለዚህ ከተራ መዓቱን አርቆ ምሕረቱን ልኮ ድኅነቱ ስለተሠጠበት ምሥጢር ይህን ትሰብክልናለች
“እንደዚህ ለአባቶቻችን ምሕረት አደረገ፤ ለአባታችን ለአብርሃምም የማለውን መሐላውን ቅዱሱን ኪዳን አሰበ”
【ሉቃስ ፩፥፸፪-፸፫】
② ይህን ከተራ ከድግል እመቤታችን ቀጥላ የሰበከችው አንቀጽ የተባለች ዮርዳኖስ ናት፤ ራሷ ቆማና ሸሽታ ከተራውን በተግባር እየመሰከረች
“አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ፥ምን ሆናችኋል?” 【መዝ ፻፲፬፥፭】
③ በጥምቀቱ የተፈጸመልንን የነገረ ከተራውን ምስክርነት ዐጻዌ ኆኅት፣ ጺያሔ ፍኖት የተባለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ለሦስተኛ ጊዜ አጽንቶታል “በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ (የሚከትር) የእግዚአብሔር በግ።”
【ዮሐ ፩፥፳፱】
ከተራ የሚለው ቃል በቁሙ ከመነሻው ከተረ ብሎ ዘጋ አቆመ አገደ ከለከለ ማለት ነው በቀረበ አውድ ደግሞ ከበበ ዐጠረ ዙሪያውን ያዘ ማለትም ይሆናል በተከበበ ገንዳ በታጠረ ሥፍራ ጥምቀቱን ከከተራ አንስተን ማክበራችን ለዚሁ ነው።
ከወንጌሉ ክፍል ለማጠቃለያ የሚሆነንን አንድ ምንባብ እናንሳና ነገረ ከተራችንን እንቋጭ
"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል። የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና"
የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲ ከቁጥር ፩―፲
በበሩ የማይገቡ «ቅዱሳን ነን ካህናት ነን» ባዮች ብዙ ወንበዴዎች አሉ። እነዚህ መዓት የማይከተርላቸው እሳተ ሲዖል የሚበላቸው የገሃነም አፍ የሚውጣቸው ናቸው። ሊቃውንቱ በሩን ወደእርሱ መግባትን ያገኘንባት እረኛችን ክርስቶስ እኛን ያገኘባት የምሥጢራቱ መግቢያ ቅድስት ጥምቀት ናት ይሉናል።
☞ ኖላዊ ኄር ዘይቤ እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ውእቱ (‹‹ቸር ጠባቂ›› ያለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።)
☞ ወአንቀጽኒ ፈለገ ዮርዳኖስ ውእቱ (‹‹በርም›› የዮርዳኖስ ወንዝ(ጥምቀት) ነው።)
☞ ወዐጻዊሰ ዮሐንስ መጥምቅ ውእቱ (‹‹በረኛውም›› ዮሐንስ መጥምቅ ነው፡፡)
☞ ወዐጸድ መንግሥተ ሰማያት ይእቲ ( ‹‹ስፍራም›› መንግሥተ ሰማያት ናት፡፡ )
አበው ሲተርቱ «ባጤ ሞት የተከተረ በስለት የተመተረ አንድ ነው» ይላሉ። ለእኛ የሕይወታችን ዐጤ የነፍሳችን ንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ ከሥፍራችን እንዳንታጣ ከቤቱ እንዳንወጣ በሞት ሳይሆን በሕይወት እንዲከትረን ከዘልዓለማዊ ዐጸድ ከሰማይ ቤቱ እንዳንጎድልና በፍርዱ ሠይፍ እንዳንመተር ከሥላሴ ልጅነታችን ከተዋህዶ ሃይማኖታችን አያናውጸን።
✍️ ፳፻፲፮ ዓ.ም. ደቡብ ሱዳን ጁባ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን የተጻፈ

᳀ #ኤጲፋንያ ᳀
᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᯼
ንወዌጥን እንከ በረድኤተ እግዚአብሔር ልዑል ፡ ወበጸሎተ እሙ ንጽሕት ድንግል ፡ ወበኃይለ ክቡር መስቀል ከመ ንጽሐፍ በእንተ ኤጲፋንያ ➨ ልዑል በሆነው በእግዚአብሔር ረድኤት : ንጽሕት ድንግል በሆነች እናቱ ጸሎት : በክቡር መስቀሉ ኃይልና አጋዥነት ስለ ኤጲፋንያ መጻፍ እንጀምራለን፤
በኦርቶዶክሳዊቷ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሳምንታዊ ወርኃዊና ዐመታዊ የበዓላት መታሰቢያዎች አሉ፤ እነዚህም በዓላት ያለፈ ፡ በዕለቱ የሆነና ሊመጣ በተስፋ የሚጠበቅ ነገር ጭምር የሚታሰቡበት ተዝካር፣ ሕዝቦችም ምሥጢሩን እያሰቡ በደስታ የሚውሉባቸው የክብር ቀናት ናቸው።
ምእመናንም የበዓላትን ቀን በመንፈሳዊ ደስታ መጠበቅና መዘከር ፡ ማግነንና ማክበር እንደሚገባ መመሪያ የሚሰጠን የሥርዓት መጽሐፋችን መጽሐፈ ዲድስቅልያ በሃያ ዘጠነኛው አንቀጽ እንዲህ ሲል ይጀምራል "ኦ ፍቁራኒሁ ለእግዚአብሔር ዕቀቡ እንከ ዕለተ በዓላት ➨ እግዚአብሔርን የምትወዱ ተወዳጆች ሆይ የበዓላትን ቀን ጠብቁ" ከዚህም ጋር በማያያዝ ከከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን ኤጲፋንያ የመከበሩን ምክንያትና እንዴት ባለ መንገድ ሊከበር እንደሚገባው ሲያስረዳ ተከታዩን ማብራሪያ አስቀምጧል
"በዓለ ኤጲፋንያ ዘቦቱ አስተርአየ እግዚአ ስብሐት ለመለኮቶ በውስተ ጥምቀቱ በኀበ ዮሐንስ በውስተ ፈለገ ዮርዳኖስ … ኤጲፋንያ የክብር ባለቤት ጌታ በዮሐንስ ዘንድ የተጠመቀበት በዮርዳኖስ ወንዝ መለኮቱን ያሳየበት በዓል ነው! (ዲድስቅልያ አንቀጽ ፳፱ ቁጥር ፫)
በሕማማቱ ሰኞ በሦስት ሠዓት በሚነበበው ግብረ ሕማማትም ይኽንኑ የቅዱሳን ሐዋርያት የሥርዓት መጽሐፍ ዲድስቅልያ በሚያሰማን ክፍል "በመንፈሳዊ ደስታ የበዓላትን ቀን መጠበቅ መፈጸም እንደሚገባ" በሚል መነሻ የተቀመጠው ምንባብ ቁጥር ፭ ላይ ኤጲፋንያ የሚለው ጥምቀቱን ተክቶ የሚከበርበት ቀን ጭምር ተመልክቶ እንደተነገረ ቀጥታ በመውሰድ የሚከበርበትን ቀን በማውሳት ነገሩን እንደሚከተለው ያጸናልናል፦
"ከዚህም በኋላ (ከበዓለ ልደቱ በኋላ) በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ ፊት የመለኮት ክብር የገለጸበትን የጥምቀቱን የኤጲፋንያን በዓል አክብሩ፤ በዕብራውያን አቆጣጠር በዓሥረኛው ወር በሰባት ቀን ሲሆን በግብጻውያን አቆጣጠር (ቀመረ ዲሜጥሮስን መነሻ ያደረገ ሊሆን ይችላል) ግን ጥር ፲፩ ቀን ይኸውም ጦቢ ማለት ጥር ነው በአምስተኛው ወር አክብሩ "
ኤጲፋንያ ለሚለው የቃሉ ምንጭ የግሪኩ ኤፒፋንያ (ἐπιφάνεια) ሲሆን መገለጥ መታየት አስተርእዮ የሚለውን ይተካል መነሻው ፌንየን (φαίνειν) ተርእየ፣ ተገለጠ ታየ ማለት ነውና። ለጌታችን ሲነገር በሰው ልጆች ሥጋ መታየቱ ከትንሳኤው በኃላ መገለጡ እና ዳግመኛ ለፍርድ መምጣቱን እየተካ በልሳነ ጽርእ ቅዱስ መጽሐፍ ተገልጧል! ግሪኩ ለሰዎች መጠሪያ ስም (ስመ ተጸውዖ) እየሠጠ ወንዱን ኤጲፋንዮስ ሴቷን ኤጲፋንያ ይላል Epiphania or Epiphaneia ( Ἐπιφανεία) is the feminine form of the name Epiphanius ) ከዚህ አያይዞ አስተርእዮን ለመለኮት መገለጥ ለአምላክ መታየት ለይቶ ለመንገር ግሪኩ ቴኦፋኒ/ቴኦፋንያ (θεοφάνεια) የሚለውን በተጨማሪነት ይጠቀማል።
በብሉይና ሐዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍትም ኤጲፋንያ የሚለው ቃል በልሳነ ጽርእ (Koine Greek)ተደጋግሞ ከአምላክ መታየት ጋር ተያይዞ ተገልጧል።
በብሉይ በመጽሐፈ መቃብያን ካልዕ "በእጃቸው ከጠላቶቻቸው ጋር ጦርነት ፡ በልባቸው ከአምላካቸው ጋር ጸሎት ይዘው ጠላት ድል ሲነሱ በእግዚአብሔር የክብር መገለጥ መደሰታቸውን" ይናገራል። ይህን መገለጥ በግሪኩ ኤጲፋንያ ብሎታል። በሐዲስ ኪዳንም በሥጋ ልደት መገለጡን ከሞት በኋላ በትንሣኤው ኃይል መታየቱን ዳግም ለፍርድ መምጣቱንም ሳይቀር ኤጲፋንያ ይለዋል።
ኤጲፋንያ የሚለው ዛሬ ላይ በምዕራባውያኑ ኬልቄዶናውያን ዘንድ ኤፒፈኒ (Epiphany) በሚል ጥምቀትን ብቻ በሚገልጽ መንገድ ይቀመጥ እንጂ ቀደምት ክርስቲያኖች አስተርእዮ መገለጥ በሚለው ትርጉሙ የሦስት ክብረ በዓላትን ምሥጢር ይዘው የበዓሉን ጥንተ ነገር ይዘከሩ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ
፩】 የክርስቶስ ጥምቀት (the baptism of Jesus)
፪】 የሰብአ ሰገል ወደ ቤተልሔም ተጉዞ አምላክን ማየት (the visit of the Wise Men to Bethlehem)
፫】 የቃና ዘገሊላው ተአምር (the miracle at Cana)
ምሥራቃውያኑ ጽባሓውያን (orientals) እና መለካውያን (Melchites) ግን እስከ ጥምቀቱ ድረስ የታየባቸውን መገለጦች ሁሉ አስተርእዮ ኤጲፋንያ ይሉታል። ከነዚህም
የልደተ እግዚእን ክብረ በዓል (celebration of Christ’s birth)፣ በሰብኣ ሰገል ክብሩ መገለጡን (the adoration of the Wisemen)፣ የጌታችን በልጅነቱ መታየቱን ከዚኽም ውስጥ በስምንተኘሰ ቀን ግዝረቱ (His circumcision) እና በዐርባ ቀን ወደ መቅደስ መውጣቱ (presentation to the temple ) እንዲሁም በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ መጠመቁ (baptism by John in the Jordan) ዋናዋናዎቹ የበዓሉ ምክንያቶች ናቸው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትውፊት ደግሞ ኤጲፋንያእና አስተርእዮ አንድነት የሚታዩ ሆነው መነሻው ከሰሙነ ጥምቀቱ ጋር ተገናኝቶ ይነገራል። ከዓመት እስከ ዓመት ያለውን የቅዱሳንን ዜና ገድልና ተዝካረ በዓል ከነማብራሪያው በአጭር በአጭር ቃል የሚዘግበው መጽሐፈ ስንክሳርም ኤጲፋንያ ከምሥጢረ ሥላሴው መገለጥ ጋር ተያይዞ እንዲህ ተገልጧል
"በዓለ ኤጲፋንያ አስተርእዮቱ ለመለኮት እስመ ባቲ አስተርአየ ምሥጢረ ሥላሴሁ ቅድስት (ልዩ የሆነች የሦስትነቱን ምሥጢር ገልጦባታልና መለኮት የተገለጠበት በዓል ማለት ነው!) Ipiphany the appearance of the Godhead,” because on this day appeared the mystery of the Holy Trinity " (ስንክሳር ጥር ፲፩ ቁ ፪)
ስንክሳሩ ተጨማሪ ሐሳብ በማከልም ከሦስቱ አካላት የአንዱ አካል የቃል/የወልድ መውረድ መታየት መገለጥ የሚታሰብበት መሆኑን ይዘግባል
በዓለ ኤጲፋንያ ዘበትርጓሜሁ አስተርእዮቱ ለመድኃኒነ ⇨ የኤጲፋንያ በዓል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ⇨ Epiphany, which is, being interpreted, the “appearance of our Our Savior (Lord Jesus)” (ስንክሳር ጥር ፲ ቁ ፮)
መጽሐፈ ሐዊ በ፶፯ኛው ባህል ደግሞ "እምነገረ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳሳት ዘእለ እስክንድርያ ዘይትነበብ በዕለተ ጥምቀት" ብሎ
«ኤጲፋንያ ዘውእቱ በዓለ አስተርእዮ በዓለ ጥምቀት ⇨ ኤጲፋንያ ይኸውም የአስተርእዮ በዓል ፣ የጥምቀት በዓል ነው» ይላል።
የቅዱሳን ሐዋርያት የሥርዓት መጽሐፍ የሆነው ሲኖዶስም ይህንኑ ሐሳብ ያጸናል

"በዓለ ኤጲፋንያ እስመ በይእቲ ዕለት አስተርአየት መለኮቱ ለክርስቶስ ፣ ኤጲፋንያ ዝ ውእቱ ሕፅበት ዘቦቱ አስተርአየ እግዚእ ወመድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኵሉ ሰብእ በፈለገ ዮርዳኖስ በብርሃነ መለኮቱ ⇨ የኤጲፋንያ በዓል በዚህች ዕለት የክርስቶስ መለኮቱ የታየ(ች)በት። ኤጲፋንያ መታጠብ ነው፤ በኤጲፋንያ ጌታ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ሁሉ በመለኮታዊ ብርሃኑ ለሰው ሁሉ በዮርዳኖስ ወንዝ የተገለጠበት ነው። 【ሲኖዶስም ትዕዛዝ ፷፮ 】
የሥርዓተ ጽዮን መጽሐፈ ቀኖና ፴ ከሚሆነው የቀኖና ክፍል በስፋት የተብራራው ስለ በዓለ ሰንበት አከባበር፣ ስለ ጾመ ጋድ (ገሐድ) እና ስለ ኤጲፋንያ በዓለ አስተርእዮ ነው።
ሠለስቱ ምዕትም በሃይማኖተ አበው ስለጾም በደነገጉት አዋጅ አጲፋንያ ጥምቀት መሆኑን አመልክተዋል።
" ወኢትትዐደው ጾመ ዘእግዚአብሔር ዘውእቶሙ ረቡዕ ወዐርብ ዘእንበለ ይርከብከ ደዌ ክቡድ ወዘእንበለ መዋዕለ ጰንጠቆስጤ ወበዐለ ልደት ወበመዋዕለ አስተርእዮ ዘውእቱ ኤጲፋንያ ➨ ጌታ ያዘዘውን ጾም አትሻር እነዚህም ረቡዕ ዓርብ ናቸው ደዌ ካላገኘህ በቀር በበዓለ ሐምሳ፣ ልደት ፣ ጥምቀት በዋሉባቸው ዕለታት (ረቡዕ ዐርብ) በቀር ይኸውም ኤጲፋንያ (ጥምቀት) ነው።" 【ሃይ. አበው ዘ፫፻ ፳፥፲፰】
በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዘመነ አስተርእዮ (Epiphany season) ዴናህ/ዴንሃ【 ܕܢܚܐ 】እየተባለ ይጠራል። በጊዜ ሰሌዳ ከጌታችን ልደት በኋላ እስከ ዐቢይ ጾም ድረስ ጾመ ነነዌንም ጭምር ይዞ ይቆያል። በዚህ ወቅት ያሉ ስምንቱን ዕለተ ዐርብ ደግሞ መታሰቢያ በመስጠት በተለየ መንገድ ያከብሩታል። የመጀመሪያው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ፣ ሁለተኛውን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ፣ ሦስተኛውን ዓርብ ለወንጌላውያን ፣ ቀጣዩን ደግሞ ለቅዱስ እጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት እያሉ የመጨረሻውን ለቤተክርስቲያን ጠባቂዎች/ ገበዝ (The Patron of the Church) ሰጥተው ያከብራሉ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም ሥርዓትና ደንብ በዚህ ወቅት በዓለ ዲያቆናት (✤ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጥር ፩) በዓለ ሐዋርያት (✤ ቅዱስ ዮሐንስ ጥር ፬) እንዲሁም በዓለ እግዝእትነ ማርያም (✤ አስተርእዮ ማርያም ጥር ፳፩) በልዩ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል።
( ክፍል ፪ ይቀጥላል… )
✍️ በዓለ ጥምቀት ፳፻፲፭ ዓ.ም. የተፃፈ